ልማት ለሁሉም፤ ሁሉም ለልማት

በበሬ ወለደ አሉባልታ የሚደናቀፍ የልማት ስራ የለም!!! ሰሞኑን በከተማችን የትራንስፖርት እንቅስቃሴን የተሳለጠ ለማድረግ ተብሎ የተላለፈው የተሻሻለ የባጃጅ ስምሪት ውሳኔን ተከትሎ አንዳንድ አሉባልታዎች እየተናፈሱ ይገኛሉ፤ እናም መጠንቀቅ ብልህነት ነው! በመሆኑም፣ “አንድ ባለሀብት 60 አውቶብስ/Bus እንዲያስገባ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ተብሎ ባጃጆችን ከከተማ ለማስወጣት ነው” በማለት እየተረገበ ያለው ወሬ መሰረት የለለው ውሸት ነው። ይህ ውሳኔ ከረጅም ጊዜ ጥናት በዃላ የተላለፈ፤ በተለይ በከተማዋ ዳር ለሚገኘው ህዝባችን የትራንስፖርት አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ የታቀደ፤ የከተማዋን የትራንስፖርት እንቅስቃሴን ማሳለጥ/Smart ማድረግን ያለመ አና የ’Smart mobility’ ግባችንን እውን በማድረግ የህዝባችንን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ መሆኑን ተገንዝበን፤ ለተፈፃሚነቱም ሁሉም ማገዝ አለበት እንላለን።

Leave a Reply